ጠ/ሚ ኃይለማርያም የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚንስትርን አነጋግሩ

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሳማህ ሀሰን ሽኩሪን በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግሩ፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ ከግብፁ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጋር በነበራቸው ቆይታ የሁለቱም ሀገራት ግንኙነት በሚጎለብትበት ሁኔታ ላይ ነው የመከሩት፡፡
ሀገራቱ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና በሌሎች የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ውይይት አድርገዋል፡፡
የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳማህ ሽኩሪን ከኢትዮጵያ አቻቸው ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋርም በጉዳዩ ላይ መክረዋል፡፡
ከውይይቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳማህ ሽኩሪን የአባይ ወንዝ ለግብፃውያን ያለው ፋይዳ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው በመሆኑ አሁንም የብሄራዊ ደህንነታቸው ጉዳይ ነው ብለዋል፡
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው ግድቡ በግብፅ ላይ የሚያሳድረው የጎላ ተፅዕኖ እንደሌለና የሁለቱም ሀገራት ህዝቦችን ጥቅም በሚያስከብር መልክ እየተከናወነ መሆኑን ለግብፁ አቻቻው አብራርተዋል፡፡
ሳማህ ሽኩሪን ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የምጣኔ ሀብት ትብብር ለማሳደግ እንደምትሰራም ተናግረዋል፡፡