የተከበሩ የኢፌዲሪ ፌደሬሽን አፈጉባኤ አቶ ያለው አባተ የተመራና የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የተካተቱበት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ስዊዘርላንድ ከሚኖሩ የዳያስፖራ አመራር አባላት ጋር የተሳካ ውይይት አደረጉ

18301371_423491944688430_6084105960163159642_n18268213_423491961355095_334407600858944688_n

የተከበሩ የኢፌዲሪ ፌደሬሽን አፈጉባኤ አቶ ያለው አባተ የተመራ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን እ.ኤ.አ ሜይ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በጄኔቭ ስዊዘርላንድ ከሚኖሩ የዳያስፖራ አመራር አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ በዚህ የውይይት ፕሮግራም የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ፣ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉዋክ ቱት ኮት ተገኝተዋል፡፡ ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚኖሩ የኮሚኒቲ አመራር አባላት እና ኢትዮጵያውያና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ውይይቱን ተካፍለዋል፡፡

18301156_423491908021767_5273057841106638149_n18221940_423492081355083_6178163375966707274_n

የኢፌዲሪ ፌደሬሽን አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ያለው አባተ እንዲሁም የክልል ርዕሰ መስተዳድሮቹ ከዳያስፖራ አባላቱ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች፣ በአባይ ጉዳይ፣ በአከባቢያችንና በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ዙሪያ፣ በመሰረተ ልማት እድገትና መስፋፋት፣ በመልካም አስተዳደርና ኪራይ ሰብሳቢነት ችግር፣ በልማት እድገት፣ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፣ በአስቸካይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጋል፡፡

18222059_423492001355091_6535799501647746705_n18268639_423492118021746_3213461292665297331_n

የኢፌዲሪ ፌደሬሽን አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ያለው አባተ በተከታታይ የተመዘገበው ፈጣን እድገት በኢትዮጵያ ህዝቦች ዘንድ ተጨማሪ ዕድገትንና ፍላጎቶችን መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡ መልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር የስርዓቱ ትልቁ አደጋ መሆኑን፣ ይህን ችግር ለመቅረፍ የልማዊና ዲሞክራሲያዊ የፖሊቲካል ኢኮኖሚ የበላይነቱን እንዲይዝ፣ ይህንኑ ዕውን ለማድረግ ደግሞ ፈጣን እድገት ማስመዝገብ እንደሚያስፈልግ፣ በገጠር የተመዘገበውን ልማት በከተማው ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑንና በቀጣይ ተጠናክሮ የሚሰራበት መሆኑን አስረድተዋል::

በዚህም ወቅት ልዩነታችን ውበታችን ከመሆኑም በላይ የጥንካሬያችን ምንጭና የአንድነታችን ምሰሶ መሆኑን በተግባር ማየትና በእያንዳንዱ ቀን ከስጋት ይልቅ ሰላምን፣ ከኋልዮሽ ጉዞ ይልቅ ተከታታይና ፈጣን እድገትን ማስመዝገብ መቻሉን የክልል ርዕሰ መስተዳድሮቹ በገለጻቸው አብራርተዋል፡፡

18274946_423492031355088_4331496249982304387_n

ከሁሉም በላይ የጋራ አመለካከቶች፣ የጋራ ስነ-ልቦና እና እምነቶች፣ እሴቶች እና  ትስስሮችና ግንኙነቶች እውን እንዲሆኑ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል ያሉት የክልል ርዕሰ መስተዳድሮቹ፣ በታሪካችን የወረስናቸው የተዛቡ ግንኙነቶችን በዲሞክራሲያዊ ግንኙነቶች በማረም የጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት እና ቀድሞ ወደነበረችበት የስልጣኔ ማማ ለማውጣት የህዳሴ ጉዞዋን በማቀላጠፍ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

18268190_423491874688437_1677274544135319683_n

በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የአገራችን ዋና ጠላት የሆነውን ድህነት ለማስወገድ መንግስት የጀመረውን የህዳሴ ጉዞና የልማት ስራዎች በመደገፍ የሚጫወቱትን የማይተካ ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ የተከበሩ የኢፌዲሪ ፌደሬሽን አፈጉባኤ አቶ ያለው አባተ በማሳሰብ ስብሰባው ተጠናቋል::