ክቡር አምባሳደር ነጋሽ ክብረት በሀንጋሪ የሥራ ጉብኝት አደረጉ

image-0-02-05-cefe687449615b07bbc3e7e96392ce5fb8f0cb78dd0f76b8c79ddb8662595c82-V

ክቡር አምባሳደር ነጋሽ ክብረት እ.ኤ.አ. ከማርች 27 እስከ ኤፕሪል 2 ቀን 2017 ዓ.ም. በሀንጋሪ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በሀንጋሪ የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ንግድ ሚኒስቴር የክቡር ቆንስላዎች ኮሚሽነር ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ የሁለቱን አገራት ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ፣ የሀንጋሪ የክብር ቆንስላዎች አስተዳደር ተሞክሮ በመቅሰም አዲስ የክብር ቆንስል ለመመልመል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሀንጋሪ አለም አቀፍ ኤርፖርት የሥራ ኃላፊ ከአገራችን አየር መንገድ ጋር ትብብር ለመፍጠር ፍላጎት እንዳለው ገልጻል፡፡

በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተዘጋጀው የቢዝነስ ፎረም ላይ የአገራችን አጠቃላይ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት፣ የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ ዕድሎችና ድጋፎች ማብራሪያ ተሰጥታል፡፡ ከካምፓኒዎች ጋር የአንድ ላንድ የቢዝነስ (B to B) ምክክር በማድረግ በአገራችን የቡድን ጉብኝት ለማድረግ ወስነዋል፡፡ ለሀንጋሪ ቱሪስት ኤጀንሲ ስለአገራችን የቱሪዝም ሀብት፣ መዳረሻዎች ማስተዋወቅ የተቻለ ሲሆን፣ የቢዝነስ ግንኙነት ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተንፀባርቃል፡፡