42ኛው የህወኃት ምስረታ በዓል በስዊዘርላንድ ተከበረ

20170218_213157

ህወኃት የተመሰረተበትና የትጥቅ ትግል የጀመረበት 42ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በስዊዘርላንድ የተለያዩ ካንቶኖች የሚገኙ  ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን፣ የደርጅቱ አባላት፣ የእህት እና የአጋር ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት ደማቅ በሆነ ዝግጅት በሎዛን ከተማ የካቲት 11 ቀን 2009 ዓ.ም ተከብራል፡፡

20170218_230202

በመጀመሪያ በስዊዘርላንድ የትግራይ ተወላጆች ማህበር ሰብሳቢ አጭር የእንካን ደህና መጣችሁ መልዕክት ተላልፋል፡፡ በመቀጠል በዚሁ የምስረታ በዓል አከባበር ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ ዮሴፍ ካሳዬ በጄኔቫ የኢ.ፊ.ዲ.ሪ. ቃሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤት ተወካይ በዓሉን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ዘንድሮው የህወኃት የምስረታ በዓል የሚከበረው በክብርና በፅናት ያለፉት ሰመአታት የህይወት ዋጋ ከፍለው የመሰረቱት የፌደራል ስርዓት እና አንግበው የተነሱበት አብዮታዊ ዲሞክራሲና ልማታዊ መስመር አማራጭ ለአገራችን አንድነትና ቀጣይነት የሚጫወተው ሚና ጎልቶ የታየበት ወቅት በመሆኑ፣ ህዝባዊ ገድላቸው ዛሬም ነገም፣ ምንጊዜም ከህዝብ ልብ አይጠፋም ካሉ በኃላ አምባገነኑ የደርግ ሥርዓት በመራራ ትግል ከተገረሰሰ በኃላ ባለፉት አስራ ሁለት ዓመታት በአገራችን ሰላም፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ማስፈን፣ የብሄር ብሄረሰቦችንና ህዝቦች እኩልነት ማረጋገጥ እንዲሁም ከፍተኛ የልማት እድገት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

20170219_003022

        በመቀጠልም ይህን ፈጣን የሆነ እድገት ግለቱ እንደተጠበቀ ለማስቀጠል፣ የአገራችንን የኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማት ውጥኖችን ለማረጋገጥ፣ የህዝብን ተጠቃሚነት እና አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባት አላማዎችን ለማሳካት አገራችን ብዙ ርቀት መጓዝ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ድህነትን ለመቀነስ፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ እድገት ቀጣይነት ይበልጥ ለማፋጠን፣ አሁን የገጠሙን የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የትምክትና የጠባብነት አመለካከትና ተግባር አደጋዎችን ለመከላከል፣ በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር የሁላችንም ተሳትፎና ጥረት ወሳኝ እንደሆነ ቃል የምንገባበት አጋጣሚ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

20170219_002940

        በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬት ለአገራችን የልማት ጉዞ ቀጣይነት የላቀ ሚና ስላለው ይህንኑ እውን ለማድረግ ሁሉም የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ቦንድ እንድንገዛ እና ሌሎችም እንዲገዙ እንዲበረታታ ጥሪያቸውን አቀርበዋል፡፡

ይህ የምስረታ በዓል በተወከልንበትና በምንኖርበት አከባቢ እንዲህ ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ ወገኖች በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በመቀጠልም በስዊዘርላንድና በትግራይ ተወላጆች ተወካይ የህወኃት ማዕከላዊ ኮሚቴ በዓሉን በማስመልከት ያወጣውን ድርጅታዊ መግለጫ በንባብ አሰምተዋል፡፡ ተወካዩ ከ17 ዓመት የትጥቅ ትግል በኃላ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በመተባበር የደርግን ስርዓት ማስወገድ መቻሉን፣ በመልካም አስተዳደር የተሰሩ ስራዎች ብዙ መሰናክሎች ቢኖሩበትም በተሀድሶ መስመር ህወኃት/ኢህአዴግ ከህዝብ ጋር በመሆን እየፈታቸው መሆኑን፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በቴክኖሎጂ ዘርፎች በርካታ ለውጦች እየመጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ድርጅቱን ለማዳከም ጽንፈኛ ሀይሎች ከውጭ የጥፋት ሀይሎች ጋር በመተባበር የፈደራል ስርዓቱን ለማፍረስና አገሪቱን ለማተራመስ የሚያደርጉትን ሙከራ ለማክሸፍ እንዲሁም በህዝቡ የተነሱ ጥያቄዎችን በአግባቡ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን  ገልጸዋል፡፡

20170218_214626

በመቀጠልም በስዊዘርላንድ በሚገኙ የኢህአዴግ እና አጋር ድርጅት ተወካዮች በኩል የአጋርነት መግለጫዎች ቀርበዋል፡፡ ህወኃት በያዘው የጠራ መስመርና በተደራጀ የዲሞክራሲዊ ንቅናቄ ላይ በመመስረት ለኢትዮጵያ ህዝቦች ነጻነትና እኩልነት እና አዲሲታን ኢትዮጵያን ለመገንባት ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በመተባበር የሰላም፣ ልማት እና ዲሞክራሲ ድሎች ለማሳካት የመሪነት ሚና መጫወቱን አውስተው፣ ለትግራይ ተወላጆችና ለመላው የህወኃት አባላት እንካን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ይሄው የሰላም፣ ልማትና ዲሞክራሲ ትግላቸው እና ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ የትምክህትና የጠባብነት አመለካከት አንግበው የፌዴራል ስርዓቱን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎችን ከህወሓት ጎን በመሆን እንደሚታገላቸው አረጋግጠዋል፡፡

20170219_003312

በመጨረሻም በዓሉን ያደመቁት ባህላዊ ምግብ፣ ጨረታና የሙዚቃ ዝግጅቶች ቀርበው የአከባበሩ ስነ ስርዓት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቃል፡፡