በስዊዘርላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን 11ኛውን ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከበሩ

 1. በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ለ11ኛ ጊዜ “ህገ-መንግስታችን ለዲሞክራሲ አንድነታችንና ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በደማቅ ሁኔታ አከበሩ፡፡ በዚህ የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ከ120 በላይ ኢትዮጵያውያና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል፡Image may contain: 12 people
 2. የሚስዮኑ ተወካይ አቶ ዩሴፍ ካሣዬ ክብረ በዓሉን አስመልክቶ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ህዳር 29 ብሄሮች በሄረሰቦችና ህዝቦች ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት የሆኑበት ቀን ብቻ ሳይሆን፣ ዘንድሮ ለ11ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ህብረ-ብሄራዊ አንድነታችን የሚያጠናክር የተሀድሶ እንቅስቃሴ እያካሄድን ባለንበት ወቅት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
  በዚህም ወቅት ልዩነታችን ውበታችን ከመሆኑም በላይ የጥንካሬያችን ምንጭና የአንድነታችን ምሰሶ መሆኑን በተግባር ማየትና በእያንዳንዱ ቀን ከስጋት ይልቅ ሰላምን፣ ከኋልዮሽ ጉዞ ይልቅ ተከታታይና ፈጣን እድገትን ማስመዝገብ መቻሉን አቶ ዮሴፍ በንግግራቸው ጠቅሰዋል፡፡
  ከሁሉም በላይ የጋራ አመለካከቶች፣ የጋራ ስነ-ልቦና እና እምነቶችን እውን እንዲሆን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል ያሉት አቶ ዮሴፍ፣ በታሪካቸው የወረሷቸው የተዛቡ ግንኙነቶችን በዲሞክራሲያዊ ግንኙነቶች ማረም መቻላቸውን፣ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት እና ቀድሞ ወደነበረችበት የስልጣኔ ማማ ለማውጣት የህዳሴ ጉዞዋን በማቀላጠፍ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡Image may contain: one or more people and people standing
 3. ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዘው ባካሄዱት ዘርፈ ብዙ ርብርብ ዓለምን ያስገረመ ፈጣንና ተከታታይ ዕድገት ማስመዝገብና በዚህም በበርካታ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከድህነት ወለል መውጣት መቻላቸውን የሚስዮኑ ተወካይ ገልጸው፣ በበዓሉ ላይ ለተሳተፉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የአገራችን ዋና ጠላት የሆነውን ድህነት ለማስወገድ መንግስት የጀመረውን የህዳሴ ጉዞና የልማት ስራዎች በመደገፍ የሚጫወቱትን የማይተካ ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡
  በአንድ በኩል በተከታታይ የተመዘገበው ፈጣን እድገት በኢትዮጵያ ህዝቦች ዘንድ ተጨማሪ ዕድገትንና ፍላጎቶችን (demand) ሲፈጥር፣ በሌላ በኩል የመንግስትን ሀብት ያለአግባብ ለግል ብልጽግና መጠቀም፣ ብልሹ አሠራሮችና ሙስና ወቅታዊ የህዝብ ጥያቄዎች መሆናቸውን ገልጸው፣ ለጥያቄዎቹ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት መንግስት ቀልጣፋና ፍትሃዊ አስተዳደር በተሻለ ደረጃ ለማረጋገጥ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመፍታት የሚረዱ በእውቀትና በቴክኖሎጂ የተደገፉ አዳዲስ የአሰራሮችንና የሙያ ድጋፎች በመስጠት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትጵያዊያን የሚያደርጉትን ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን በመግለጽ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
  ዲሞክራሲያዊ አንድነት እንዲበለጽግ እጅግ አበረታች ስራዎችን መሰራታቸውን ገልጸው፣ በሌላ በኩል ደግሞ ይህን እሴት የሚጎዱ ተግባራትም በጠባብነትና በትምክህት አስተሳሰቦች በመነዳት ጉዳቶች ሲያስከትሉ መስተዋሉንን ገልጸው፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትጵያዊያን በጥፋት ሀይሎች የሚከናወኑ አፍራሽ እንቅስቃሴዎችን በማጋለጥ የሚጫወቱትን ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡
 4. Image may contain: 5 people, people sitting
  በዓሉን የምናከብረው ህገ-መንግስታችን ያስገኘልን ተስፋ ሰጪ ድሎችን አጎልብቶ ለማስቀጠል፣ የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ ለማጠናከር፣ የጠባብነትና የትምክህት አስተሳሰቦችና ዝንባሌዎች ምንጭ፣ መገለጫዎችና ስትራቴጂዎች በውሉ ተገንዝቦ ለመመከት፣ የተጀመረውን የልማት፣ ዲሞክራሲና የህዳሴ ጉዞ ከዳር ለማድረስ፣ ከሁሉም በላይ የልማታችንና የሰላማችን ዋስትና የሆነውን ህገ-መንግስታችንን ከማንኛውም አደጋ ለመጠበቅ ቃላችንን በማደስ ነው ብለዋል፡፡
  የበዓሉ ተሳታፈዎች በበኩላቸው የብሄር ብሄረሰቦችን በዓል የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የምናጠናክርበት፣ እኩል ተሳትፎና የጋራ ተጠቃሚነት የምናጎላበት፣ ያገኘናቸውን ድሎች አጠናክረን የምንቀጥልበት እና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የምንሰራበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በሚስዮኑ ተወካይ ጋባዥነት የተለያዩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ተወካዮች የሻማ ማብራትና የዳቦ ቆረሳ ሥነ-ስርዓት አካሂደዋል፡ በዓሉን አስመልክቶ ዴሞክራሲያዊ ብሄረተኝነትና ሕብረ-ብሄራዊነት በኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓት በሚል ርዕስ ገለጻና ውይይት ተደርጓል፡፡
  Image may contain: one or more people and people standing
 5. የዲሞክራሲ ብሄረተኝነትና ህብረብሄራዊነት ተፈጻሚ በማድረግ የተገኙ ስኬቶች (በፖለቲካ፣ በሰላምና መረጋጋት፣ በልማት፣ ዘርፎች) በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ በተለይም የብዙሃን አያያዝ የአገሪቱን ሰላም ማስፈንና ሁለንተናዊ ዕድገት በማፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረጉን ተገልጿል፡፡ በብዘሃነት አያያዝ ላይ የሚታይ በአፈጻጸም ሂደት እየተከሰተ ያሉ ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በዝርዝር ቀርቧል፡  በዚሁ በዓል ላይ ባህላዊ ምግብ በሐረሪና በሶማሊ ኮሚኒቲ ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን፣ በኮሚኒቲው የሴቶች ሊቀ-መንበር ወ/ሮ ሰዓዳ ፈሲህ ስለ ሐረሪ ባህል ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡