ኢትዮጵያዊ ዜግነት ባላቸው ባለሀብቶች ብቻ የሚካሄዱ የስራ መስኮችን ስለማሳወቅ

የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 270/94 አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ 5 ስር ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንደ አገር ውስጥ ባለሀብት መቆጠር ከፈለጉ በአገሪቱ የኢንቨስትመንት ህግ መሠረት ለአገር ውስጥ ባለሀብት በተፈቀዱ የኢንቨስትመንት መስኮች መሳተፍ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ነገር ግን የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለከሉ የስራ መስኮች በሚል ባወጣው ደንብ ቁጥር 270/2005 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 1 ስር ኢትዮጵያዊ ዜግነት ባላቸው ባለሀብቶች ብቻ የሚካሄድ የስራ መስኮች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡ እነርሱም፡-

ሀ. የባንክ፣ የኢንሹራንሽ እና አነስተኛ የብድርና ቁጠባ ተቋም ስራዎች፣
ለ. ዕቃዎችን የማሸግ፣ የማስተላለፍና የመረከብ ውክልና አገልግሎት፣
ሐ. የብሮድካስቲንግ ስታ፣
መ. የመገናኛ ብዙሃን ስራዎች፣
ሠ. የጥብቅናና የህግ ማማከር አገልግሎት፣
ረ. አገር በቀል ባህላዊ መድሀኒቶችነ ማዘጋጀት፣
ሰ. የማስታወቂያ፣ የፕሮሞሽንና የትርጉም ስራዎች፣
ሸ. እስከ 4 መንገደኞችን የመጫን አቅም ባለው አውሮፕላን የሚሰጥ የአየር ውስጥ የመንገደኞች የአየር ትራንስፖርት የሚሉት ናቸው፡፡

ስለሆነም ዜግነታቸውን የቀየሩ የዳያስፖራ አባላት የትውልድ ኢትዮጵያውያን ከሀ-ሸ በተገለጹት የኢንቨስትመንት መስኮች መሰማራት እንደማይችሉ እያስታወቅን ለበለጠ ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ከላይ የተጠቀሰውን ደንብ ሶፍት ኮፒ ከታች የሚታየውን ሊንክ በመጫን መመልከት እንደሚችሉ እንገልጻለን፡፡

https://mail.google.com/mail/u/0/h/4v7bwot2rxkb/…